ሩህ ሚዲያ – Ruh Media

Find articulated views on the Fabrics of Ethiopian society & the world at large. There is no limit of topics of address: culture, lifestyle, history, art, literature, politics and economy. Habtamu Girma's page shares opinions, viewpoints, and/or commentaries on issues that matters for us all!!!

ሩህ ሚዲያ የተለያዩ የዲጂታል የብዝሃ-መገናኛ አማራጮችን በመጠቀም በአፍሪካ፣ በተለይ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ አስተዳደርና ፖሊሲ፣ ፖለቲካል ኢኮኖሚ፣ ጂኦ-ኢኮኖሚክስ፣ ጂኦ-ፖለቲካ ጉዳዮች ዙሪያ በእውቀትና በዕውነት የተቀረጹ መረጃዎችን ለህዝብ ማድረስን ዓላማው ያደረገ ሚዲያ ነው፤ ዓላማውም በአገራዊ ኢኮኖሚያዊ አጀንዳዎች ላይ የሚኖረን ግንዛቤ በጥናትና በዕውቀት የተደገፈ እንዲሆን ጥረት ማድረግ ነው፤ በሩህ ሚዲያ ውስብስብ የሆኑ የኢኮኖሚ ጽንሰ ሃሳቦች እና የፖሊሲ እርምጃዎችን በቀላሉ ህዝብ በሚረዳው መንገድ ለማቅረብ ጥረት ይደረጋል // Ruh Media is aimed at addressing contextual factors associated to African economy, politics, geo-economics, natural resource conservation & management, climate change and energy transition issues. Ruh Media produces original contents capturing the human stories behind statistics, and showing how continental (African) and Ethiopian specific developmental aspirations translate into community-level change // የሩህ ሚዲያ ድህረ ገጽና የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን ይጎብኙ፤ ይወዳጁ!

በኮሮና ቫይረስ ላይ ያለን ቸልተኝት የሚያስከፍለን  ዋጋ ምን ያህል ይሆን ?

ሀብታሙ ግርማ፤ መጋቢት 14 ቀን 2012 ዓ.ም፤ ጅግጅጋ፣ ኢትዮጵያ

መግቢያ

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ሂሳባዊ ቀመር የዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ በ March 15,2020 እትሙ ይዞ ወጥቷል።በዚህች አጭር ጽሑፍ የጥናቱን ግኝት (findings) አጠቃሎ (Summary) ለማቅረብ እሞክራለሁ።

የዚህ ጽሑፍ መነሻ ፦ በአሜሪካ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት(March 13,2020 በአገሪቱ በነበረው የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር በመመርኮዝ) የተደረገ አንድ ጥናት ላይ ተመርኩዞ የጥናቱን ግኝት (findings) እና ምክረ ሃሳብ (Recommendations) አጠቃሎ ማቅረብ ነው።

ከይዘት አኳያ፦ ይህ ጽሑፍ የጥናቱን ውጤት ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ አኳያ ለመተርጎም ይሞክራል። በመሆኑም በኢትዮጵያ በሚቀጥሉት ሁለት ወራት እና በቀጣዮቹ ሌሎች ሁለት ወራት የሚኖረውን የበሽታውን የስርጭት እና የሞት መጠን ትንበያ ለመጠቆም ተሞክሯል።

የዚህ ጽሑፍ አላማ፦ መዓት መጥራት ሳይሆን ቸልተኝነት የሚያስከትለውን ዋጋ ለህዝብ ማሳወቅ ነው፤ በመሆኑም ቸልተኝነቱ በዚሁ ከቀጠለ የኮሮና በሽታ ስርጭት መጠንን በማሳወቅ የኢትዮጵያ ህዝብ ከተጋረጠበት የእልቂት አደጋ ራሱን ይጠብቅ ዘንድ ነው።

የጽሑፉ ጭብጥ፦ መራራቅ (social distancing) እንዴት ከበሽታው መስፋፋት እንደሚታደገን ነው።

የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እና ሞት መጠን ትንበያ (Using Simulation Technique of Estimation)

በአሜሪካ የሚገኘው Johns Hopkins University Center for Systems Science and Engineering ጥናት መሰረት በአገሪቱ እስከ March 13,2020 ድረስ በኮሮና የተያዙ ሰዎች ቁጥር 2179 ነው። የዋሽንግተን ፖስቱ ጸሐፊ Harry Stevens በዚህ አሃዝ ተመርኩዞ በአሜሪካ ሰዎች ራሳቸውን ሰውረው የማይቀመጡ ከሆነ የበሽታውን የሥርጭት እና ሞት መጠን እንደሚያስከትል አንድ ጽሑፍ አስነብቦናል።

በዚህ ጽሑፍ እንደተገለጸው የበሽታው ስርጭት የሚለካው በሒሳብ ሳይንስ Geometric Progression የሚባለው የብዜት ልኬት(Multiplication factor) ነው። በጥናቱ የበሽታው ከሰው ወደ ሰው የመተላለፉን ፍጥነት እና መጠን የቀረበው Simulation Technique በሚባለው ዘዴ ነው። ሙሉ የጥናት ዘገባውን ከሚከተለው ሊንክ ያገኛሉ

https://www.washingtonpost.com/graphics/2020/world/corona-simulator/?fbclid=IwAR2bh1-JEFMvWgver89gjhF2OJI_Jk3a0JCQ2Sxx251uTVnEqUC1o10sCDk

የጥናቱ ግኝት

በየሶስት ቀኑ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በእጥፍ ይጨምራሉ፤

በዚህ መሰረት ሰዎች ራሳቸውን ከማህበራዊ መሰተጋብር ካላራቁ በአሜሪካ እስከ May 2020 (በሁለት ወራት) መቶ ሚሊዮን ሰዎችን ያጠቃል ማለት ነው።

የአሜሪካ ህዝብ ቁጥር በMay 2020 331 ሚሊዮን ይገመታል። በመሆኑም ህዝቡ ራሱን ከማህበራዊ መስተጋብር የማያርቅ አሜሪካ ሲሶ (1/3 ኛ) የሚሆነው ህዝቧ በበሽታው ይያዛል።

የበሽታው ሥርጭት ፍጥነት መግታት ካልተቻለ እስከ መስከረም ወር መጨረሻ መላውን የአሜሪካ ህዝብ በኮሮና ቫይረስ ይጠቃል ማለት ነው።

በኢትዮጵያ የኮሮና ስርጭት ትንበያ (ከመጋቢት እስከ ነሐሴ 2012 ዓ.ም)

120 ሚሊዮን ገደማ ህዝብ ባላት ኢትዮጵያ እስካሁን ምን ያህል ህዝብ እንኳ እንደተያዘ በትክክል አይታወቅም፤ በሽታው ቶሎ ራሱን የማይገልጥ መሆኑ፣ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የሚያስችል ተቋማዊ፣ ሎጀስቲካዊ፣ የፋይናንስ እንዲሁም የባለሙያ እጥረት ባለባት ኢትዮጵያ በሽታው መዛመት እጅግ አስፈሪ እንደሚሆን መገመት አይከብድም።

የሆነው ሆኖ ከዚህ በታች የመለከተው ትንበያ የተሰራው በኢትዮጵያ በMarch 13,2020 የኮሮና ተጠቂ ህዝብ ቁጥር 2179 ነው የሚል ማንበሪያ (Assumption) በመውሰድ ነው።በተጨማሪም ስሌቱ የተሰራው ህዝቡ ከማህበራዊ መስተጋብር ራሱን ካላራቀ (Social distancing) ካልተከተለ በሚል የተወሰደ ነው።

የበሽታው ሥርጭት በኢትዮጵያ

እንበልና በኢትዮጵያ March 13 2020 በኮረና የተያዙ ሰዎች ቁጥር 2179 ነው።

ህዝቡ የማህበራዊ መስተጋብር (Social distancing) መርህን ተከትሎ ህይወቱን የማይመራ ከሆነ በኢትዮጵያ እስከ ግንቦት ወር መጨረሻ ድረስ በኮሮና በሽታ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር አርባ (40) ሚሊዮን ይደርሳል።

አሁንም ህዝቡ በውድም ሆነ በግድ እንቅስቃሴውን መገደብ ካልተቻለ እስከ ነሐሴ ወር መጨረሻ (በሚቀጥሉት አራት ወራት) ሁሉም በኢትዮጵያ የሚኖር ህዝብ በኮሮና ቫይረስ ይያዛል።

እንግዲህ ከላይ የተመለከተው የበሽታው ስርጭት እና ሞት አሃዝ ታሳቢ ያደረገው ህዝብ ከእንቅስቃሴው ሳይገታ የተለመደ እንቅስቃሴውን ካልተወ ነው።

በኮሮና በሽታ ከተያዙ ሰዎች 4% የሚሆኑት መሞት እድላቸው የሰፋ እንደሆነ የጤና ባለሙያዎች ጥናት ይነግረናል። በመሆኑም ሊከሰት የሚችለው የሞት መጠን በበሽታው የተያዙ ሰዎችን በተቻለ መጠን በመቀነስ ነው። ይህ እንዲሆን ደግሞ ሰዎች በራሳቸው ተነሳሽነት ወይም ተገደው በቤታቸው እንዲቀመጡ ማድረግ ብቸኛው አማራጭ ነው።

አላስፈላጊ የቤት ውጪ እንቅስቃሴን በማስወገድና ብዙ ጊዜን በቤት ውስጥ በመቆየት የበሽታውን ሥርጭትም ሆነ የሞት መጠንን በትልቁ መቀነስ ይቻላል።

የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት ለመግታት እና ከእልቂት እንተርፍ ዘንድ የማህበራዊ መስተጋብራችንን እንቀንስ!

እንግዲህ ልብ ያለወሰ ልብ ይበል!!!


Discover more from ሩህ ሚዲያ – Ruh Media

Subscribe to get the latest posts sent to your email.

Posted in

አስተያየት ያስቀምጡ

ይህ ጣቢያ አይፈለጌ መልዕክትን ለመቀነስ Akismet ይጠቀማል። የአስተያየትዎ ውሂብ እንዴት እንደሚሰናዳ ይወቁ

Discover more from ሩህ ሚዲያ - Ruh Media

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading