ሩህ ሚዲያ – Ruh Media

Find articulated views on the Fabrics of Ethiopian society & the world at large. There is no limit of topics of address: culture, lifestyle, history, art, literature, politics and economy. Habtamu Girma's page shares opinions, viewpoints, and/or commentaries on issues that matters for us all!!!

ሩህ ሚዲያ የተለያዩ የዲጂታል የብዝሃ-መገናኛ አማራጮችን በመጠቀም በአፍሪካ፣ በተለይ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ አስተዳደርና ፖሊሲ፣ ፖለቲካል ኢኮኖሚ፣ ጂኦ-ኢኮኖሚክስ፣ ጂኦ-ፖለቲካ ጉዳዮች ዙሪያ በእውቀትና በዕውነት የተቀረጹ መረጃዎችን ለህዝብ ማድረስን ዓላማው ያደረገ ሚዲያ ነው፤ ዓላማውም በአገራዊ ኢኮኖሚያዊ አጀንዳዎች ላይ የሚኖረን ግንዛቤ በጥናትና በዕውቀት የተደገፈ እንዲሆን ጥረት ማድረግ ነው፤ በሩህ ሚዲያ ውስብስብ የሆኑ የኢኮኖሚ ጽንሰ ሃሳቦች እና የፖሊሲ እርምጃዎችን በቀላሉ ህዝብ በሚረዳው መንገድ ለማቅረብ ጥረት ይደረጋል // Ruh Media is aimed at addressing contextual factors associated to African economy, politics, geo-economics, natural resource conservation & management, climate change and energy transition issues. Ruh Media produces original contents capturing the human stories behind statistics, and showing how continental (African) and Ethiopian specific developmental aspirations translate into community-level change // የሩህ ሚዲያ ድህረ ገጽና የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን ይጎብኙ፤ ይወዳጁ!

ኮሮና ወረርሽኝ ሳይሆን ጦርነት ነው፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለዘመቻ ራሱን ያዘጋጅ!

ሀብታሙ ግርማ
መጋቢት 5 ቀን 2012 ዓ.ም
ድሬዳዋ፣ኢትዮጵያ



የሚቻል አይደለም እንጂ የኮሮና ቫይረስ እንዳይገባ ማድረግ ብንችል መልካም ነበር። ነገር ግን አለም የመንደር ያህል በጠበበችበት ዛሬ (አየር መንገድን መውቀስ አይቻልም!) ይህ የሚቻል አይደለምና የኮሮና ቫይረስ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ ዛሬ ይፋ ሆኗል።

ከዚህ በኋላ እንዴት የዚህን በሽታ መስፋፋት እንዴት መግታት ይቻላል የሚለው ላይ ማተኮር ነው የሚያሻው፤ ለዚህ ደግሞ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ማድረግ ስላለበት ነገር ጥቂት ልበል፦

* በቅድሚያ ራሳችንን በጦርነት ላይ እንዳለን ማሳመን፣

* የውጊያው ስንቅ የሚሆነው የውጊያ መንፈስ ነው፤ እናም ለዘመቻው መዘጋጀት፤ ይህም ሲባል ከመደንገጥ እና ከመረበሽ ይልቅ በወኔ እና በአገር ፍቅር ስሜት ለውጊያው ራስን ማዘጋጀት

የውጊያው ዋነኛ ትጥቅ ስለበሽታው አጠቃላይ ግንዛቤ መጨበጥ፣ ማስጨበጥ እና ማስረጽ ነው

* የውጊያው መሪ ሁሉም ነብስ ያወቀ ኢትዮጵያዊ ይሆናል፤

የውጊያው ስልት የአልሸነፍ ባይነት ወኔ እና እምነት ናቸው። ከታሪካችን ማህደር እንደምናገኘው አባቶቻችን በአውደ ውጊያዎቻቸው እንዳደረጉት በእጃቸው ጦር እና ጋሻ፣ በልቦናቸው ደግሞ የፈጣሪን ተራዳኢነት ይዘው ነበር። ኮሮናን ለመግጠም ስንዘጋጅ እኛም ተመሳሳይ ስልት መከተል አለብን።

ስለሆነም፣ ዝቅ ሲል ራስን እየተከላከሉ የበሽታውን መስፋፋት መከላከል፣ከፍ ሲል ስርጭቱን ለመግታት ማጥቃት ነው፤ ኢትዮጵያዊያን ጦርነት ላይ እጅ መስጠት ታሪካችን አይደለምና ኮሮናን በመዋጋት ሂደት የሚከፈለውን መስዋዕትነት ለመክፈል መዘጋጀት ያሻል፤ ሞቶ ሌሎችን ለማዳን የመንፈስ ዝግጁነት ይጠይቃል

* ከዚህ በመለስ ሁሉን ለፈጣሪ መተው፣ መልካም ማሰብ፣ መልካም ማድረግ መፍትሄ ነው!


ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአገር ፍቅር እና ህዝባዊ መንፈስ ኮሮናን ለመግጠም ወደፊት!


Discover more from ሩህ ሚዲያ – Ruh Media

Subscribe to get the latest posts sent to your email.

Posted in

አስተያየት ያስቀምጡ

ይህ ጣቢያ አይፈለጌ መልዕክትን ለመቀነስ Akismet ይጠቀማል። የአስተያየትዎ ውሂብ እንዴት እንደሚሰናዳ ይወቁ

Discover more from ሩህ ሚዲያ - Ruh Media

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading