ሩህ ሚዲያ – Ruh Media

Find articulated views on the Fabrics of Ethiopian society & the world at large. There is no limit of topics of address: culture, lifestyle, history, art, literature, politics and economy. Habtamu Girma's page shares opinions, viewpoints, and/or commentaries on issues that matters for us all!!!

ሩህ ሚዲያ የተለያዩ የዲጂታል የብዝሃ-መገናኛ አማራጮችን በመጠቀም በአፍሪካ፣ በተለይ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ አስተዳደርና ፖሊሲ፣ ፖለቲካል ኢኮኖሚ፣ ጂኦ-ኢኮኖሚክስ፣ ጂኦ-ፖለቲካ ጉዳዮች ዙሪያ በእውቀትና በዕውነት የተቀረጹ መረጃዎችን ለህዝብ ማድረስን ዓላማው ያደረገ ሚዲያ ነው፤ ዓላማውም በአገራዊ ኢኮኖሚያዊ አጀንዳዎች ላይ የሚኖረን ግንዛቤ በጥናትና በዕውቀት የተደገፈ እንዲሆን ጥረት ማድረግ ነው፤ በሩህ ሚዲያ ውስብስብ የሆኑ የኢኮኖሚ ጽንሰ ሃሳቦች እና የፖሊሲ እርምጃዎችን በቀላሉ ህዝብ በሚረዳው መንገድ ለማቅረብ ጥረት ይደረጋል // Ruh Media is aimed at addressing contextual factors associated to African economy, politics, geo-economics, natural resource conservation & management, climate change and energy transition issues. Ruh Media produces original contents capturing the human stories behind statistics, and showing how continental (African) and Ethiopian specific developmental aspirations translate into community-level change // የሩህ ሚዲያ ድህረ ገጽና የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን ይጎብኙ፤ ይወዳጁ!

አብይ አህመድን መውቀስ ተገቢነቱ ከምርጫ በኋላ ነው!

ሀብታሙ ግርማ
ጥር 19 ቀን 2012 ዓ.ም
ጅግጅጋ፣ኢትዮጵያ



የጽሑፌ መነሻ አቶ ልደቱ በአብይ አህመድ የአመራር ብቃት ላይ በአስራት (ASRAT) ቴሌቭዥን የሰጠው አስተያየት ነው (ከታች ምስሉን ይመልቱ)። በእኔ አተያይ አስተያየቱ በራሱ ቅንነት የጎደለው ነው። ምክንያቱም አቶ ልደቱ በኢትዮጵያ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ እያወቀ እንደማያውቅ ሆኖ የተናገረው ነው።

መሪያችን በስንት ገመድ እየተጎተተ እንዳለ እንኳን እንደ አቶ ልደቱ አያሌው ያለ አንጋፋ ፖለቲከኛ ለማንኞውም ዜጋ የተሰወረ ሀቅ አይደለም።

ብሔርተኞች በየፈርጃቸው ፍላጎታቸውን እንዲያስፈጽምላቸው ሲውተረተሩ፣ ህወሓት በውስጠ ፓርቲ ቅራኔ ፌዴራል ሥርዓቱን ለማዳከም ቀን ከሌት እየሰራ ባለበት ሁኔታ ይህ ሰው ብቻውን በብልሃት እና በጥበብ ፈተናዎቹን በአግባቡ እያለፈ ያለ መሪ ነው።

አብይ ከብዙ አቅጣጫ እየተጋፈጠ ያለው የገመድ ጉተታ እልባት የሚያገኘው፣ በዚህም ከተለያዩ ዋልታ ረገጥ ፖለቲካዊ ፍላጎቶች ተጽዕኖ ተላቅቆ የሚያስወቅስም ሆነ የሚያስመሰግን ውሳኔ ሊወስን የሚችለው ከምርጫው በኋላ ነው።

በእኔ እምነት በዚህ ሰዓት እንደ አብይ አህመድ የብዙሃንን ፍላጎት አስማምቶ የመምራት ብቃትም፣ ጽናት እና ቅቡልነት ያለው መሪ የለም። ይህን ስል ግን አብይ ከፈጣሪ የተላከ መልአክ፣ ተኪ የሌለው መሪ ነው ማለቴ አይደለም።

አብይ አህመድን እንደ መንግስት ለመውቀስ ተገቢ የሚሆነው ከምርጫው በኋላ ነው። ያኔ ጠቅላዩ ሙሉ ስልጣኑን ወይ ያሸንፋል ወይም አሁን በወቀሳ የተጠመድን ዜጎችም ሆነ ፖለቲከኞች መንግስት ለሚመሰርተው አካል በህግ የመገዛት ግዴታ የሚኖርብን ይሆናል። ለሁሉም የሚወስነው ጊዜና ጊዜ ብቻ ነው። እድሜ ይስጠንና ሁሉንም እናያለን።

ነገር ግን የነገ እጣ ፈንታችንን የሚወስነው የዛሬ ውሳኔያችን ነውና የማንዐጸትበት ውሳኔ እንድንሰጥ ይገባል። የማንጸጸትበት ውሳኔ ማለት ውሳኔያችን የሚያስከትለውን በጎም ሆነ አሉታዊ ገጽ ለመቀበል መዘጋጀት ማለት ነው። አንዴ ከወሰንን በኋላ ይህ በሆነ ኖሮ፣ ኖሮ፣ ኖሮ አይሰራም።


Discover more from ሩህ ሚዲያ – Ruh Media

Subscribe to get the latest posts sent to your email.

Posted in

አስተያየት ያስቀምጡ

ይህ ጣቢያ አይፈለጌ መልዕክትን ለመቀነስ Akismet ይጠቀማል። የአስተያየትዎ ውሂብ እንዴት እንደሚሰናዳ ይወቁ

Discover more from ሩህ ሚዲያ - Ruh Media

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading