ሀብታሙ ግርማ
ጥር 5 ቀን 2012 ዓ.ም
ጅግጅጋ፣ ኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ የጊዜው አሳሳቢ የጤና እክል የኩላሊት ስራውን የማቆም በሽታ (End-Stage Renal Disease (ESRD) ነው። በሽታው በአብዛኛው በከተማው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ፣ በተለይም አምራች የሰው ሀይል ክፍልን በስፋት እያጠቃ ይገኛል።
አንባቢያን የህመሙ ምክንያቶች፣ ምልክቶች፣ የህክምና አማራጮች፣ እና የጥንቃቄ ምክር ከሚከተለው ሊንክ ሊያገኙ ይችላሉ፦ https://www.kidneyfund.org/kidney-disease/kidney-failure/
የጤና ባለሙያ ስላልሆንኩ ስለጉዳዩ ትንተና መስጠት አልችልም። ነገር ግን በአጭር ጊዜ በሽታው አጣዳፊ የማህበረሰብ ጤና እክል ደረጃ የመድረሱ ነገር ከጤና ባለፈ የፖለቲካል-ኢኮኖሚ ገጽታ ይኖረው ይሆን የሚል ጥያቄን አጭሮብኛል።
በእርግጥም መንግስት እና ለመንግስት ቅርበት ያላቸው ነጋዴዎች ባለፉት አመታት በምግብ እና ምግብ ነክ ምርቶች እንዲሁም በመድሃኒት ንግድ ላይ በስፋት መሳተፋቸው በምርቶቹ ጥራት ቁጥጥር ላይ የራሱ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረው እገምታለሁ። ይህም ማህበረሰቡን እንደ ኩላሊት ያሉ ገዳይ በሽታዎች ተጋላጭ የሚሆንበትን ዕድል ማስፋቱ የማይቀር ነው።
ከዚህ አንጻር እነዚህ ከታች የማነሳቸው ነጥቦች ማየት
ያሻል፦
በሽታው እንዲህ በአጭር ጊዜ የመንሰራፋቱን ጉዳይ መንግስት ጉዳዩ በሚፈልገው ልክ ምላሽ ያለመስጠቱ ምክንያት ምን ይሆን?
ስለ በሽታው ማህበረሰባዊ ግንዛቤ ከማስጨበጥ ይልቅ ወ
ወይም ከመከላከል ይልቅ ለማከም የሚደረገው ሩጫ ጎልቶ የመታየቱ ነገር ቢፈተሽ፤ ከዚህ አንጻር የዲያሊሲስ ህክምና ውድነት ህክምናው እንደ ቢዝነስ እድል የመጠቀሙ ነገር አዝማሚያ ይኖራል።
መንግስት የአገር ድንበርን ለመጠበቅ ሰራዊት አሰልጥኖ እንደሚያሰማራው ሁሉ ዜጎቹን እንደ ኩላሊት ህመም አይነት ገዳይ በሽታዎች የመጠበቅ ግዴታ አለበት። ከዚህ አንጻር በሽታው በአመጋገብ ስርዓት እና/ወይም መሰረታዊ የምግብ ማዘጋጃዎች እንደ ዘይት፣ ቅመማ ቅመሞች፣ የምግብ ማሸጊያ እቃዎች፣ የምግብ እና ምግብ ነክ እቃዎች የምርት ጥራት፣ የአገልግሎት ዘመን ክትትል፣ የሚጓጓዙበት እና የሚከማቹበት ሁኔታ ተገቢው ክትትል እና ቁጥጥር መደረግ አለበት።

አስተያየት ያስቀምጡ