• This Time, Abiy Ahmed has Surrendered!

    Habtamu Girma
    March 14/2020
    Dire Dawa, Ethiopia


    This time, Abiy has surrendered! And he gave in to applauds of men who gave him penny for his ‘prosperity party’. He insulted an idea, and I don’t know how he will make of it!

    For a while, I never have aspired a strong man would fell into the elbow of few without content. What happened to Abiy Ahmed is still unclear. But, his words would be so striking that he reiterated his predecessors’ in humiliating the power of knowledge!

    At the end, he will pay the price. Sad to hear such astounding words from a person I trusted as a right leader. But, I am glad that I have never branded him as true leader!.

    In the end, Abiy fell in for money! That is shame on him. Same people he was in front of them today were ones who raised millions for EPRDF in those ‘good days’!

    It is ironic that Abiy has just showed up for the power of money, that money is powerful enough to switch one’s stand! Abiy has showed it up!!!


    ABIY IS YET TO BE A TRUE LEADER !!!

    For a while, I came to understand that Abiy neither a right leader; nor a true leader! At the moment, he is confused!


  • ኮሮና ወረርሽኝ ሳይሆን ጦርነት ነው፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለዘመቻ ራሱን ያዘጋጅ!

    ሀብታሙ ግርማ
    መጋቢት 5 ቀን 2012 ዓ.ም
    ድሬዳዋ፣ኢትዮጵያ



    የሚቻል አይደለም እንጂ የኮሮና ቫይረስ እንዳይገባ ማድረግ ብንችል መልካም ነበር። ነገር ግን አለም የመንደር ያህል በጠበበችበት ዛሬ (አየር መንገድን መውቀስ አይቻልም!) ይህ የሚቻል አይደለምና የኮሮና ቫይረስ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ ዛሬ ይፋ ሆኗል።

    ከዚህ በኋላ እንዴት የዚህን በሽታ መስፋፋት እንዴት መግታት ይቻላል የሚለው ላይ ማተኮር ነው የሚያሻው፤ ለዚህ ደግሞ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ማድረግ ስላለበት ነገር ጥቂት ልበል፦

    * በቅድሚያ ራሳችንን በጦርነት ላይ እንዳለን ማሳመን፣

    * የውጊያው ስንቅ የሚሆነው የውጊያ መንፈስ ነው፤ እናም ለዘመቻው መዘጋጀት፤ ይህም ሲባል ከመደንገጥ እና ከመረበሽ ይልቅ በወኔ እና በአገር ፍቅር ስሜት ለውጊያው ራስን ማዘጋጀት

    የውጊያው ዋነኛ ትጥቅ ስለበሽታው አጠቃላይ ግንዛቤ መጨበጥ፣ ማስጨበጥ እና ማስረጽ ነው

    * የውጊያው መሪ ሁሉም ነብስ ያወቀ ኢትዮጵያዊ ይሆናል፤

    የውጊያው ስልት የአልሸነፍ ባይነት ወኔ እና እምነት ናቸው። ከታሪካችን ማህደር እንደምናገኘው አባቶቻችን በአውደ ውጊያዎቻቸው እንዳደረጉት በእጃቸው ጦር እና ጋሻ፣ በልቦናቸው ደግሞ የፈጣሪን ተራዳኢነት ይዘው ነበር። ኮሮናን ለመግጠም ስንዘጋጅ እኛም ተመሳሳይ ስልት መከተል አለብን።

    ስለሆነም፣ ዝቅ ሲል ራስን እየተከላከሉ የበሽታውን መስፋፋት መከላከል፣ከፍ ሲል ስርጭቱን ለመግታት ማጥቃት ነው፤ ኢትዮጵያዊያን ጦርነት ላይ እጅ መስጠት ታሪካችን አይደለምና ኮሮናን በመዋጋት ሂደት የሚከፈለውን መስዋዕትነት ለመክፈል መዘጋጀት ያሻል፤ ሞቶ ሌሎችን ለማዳን የመንፈስ ዝግጁነት ይጠይቃል

    * ከዚህ በመለስ ሁሉን ለፈጣሪ መተው፣ መልካም ማሰብ፣ መልካም ማድረግ መፍትሄ ነው!


    ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአገር ፍቅር እና ህዝባዊ መንፈስ ኮሮናን ለመግጠም ወደፊት!

  • ETHIOPIAN VALUES CANNOT BE EXCHANGED FOR DOLLARS!

    With a Clear Double Standards on Global Affairs, Donald Trump Cannot Keep America Great Again!


    Habtamu Girma
    March 5, 2020
    Jigjiga, Ethiopia


    The Absurd Donal Trump trying to Play both Roles, as an Arbitrator and a Jury on Disputing GERD, a Flagship Dam Project for Ethiopians

    The US based Financial Times Newspaper, in its March 5/2020 issue reads that US Ready to back Ethiopia’s Reform with $5 billions Investment. The 5 billions of dollars provided must be for mutual benefit of both countries, Ethiopia and USA. Indeed that if the US firms come to Ethiopia, it must only be for shared economic interests between Ethiopia and USA. No more no less!

    HEADLINE FROM FINANCIAL TIMES, MARCH 5/2020 ISSUE

    If there is a string attached with the billions of dollar which threatens the sovereignty of Ethiopia or defy the values of Ethiopians, let them go back with their money!

    USA has to be clear with Ethiopian values and history, that we never ever put our freedom and sovereignty to sale. In this regard, the recent stand of USA against the Great Ethiopian Renaissance Dam, a flagship project for us, is unacceptable.

    Ethiopians are very concerned about US stance on GERD. Trump adminstration was illusive of its role in the recent negotiations with Egypt, both as an arbitrator and a judge. His move amounts humiliating our existence as a sovereign nation. That is shame on America, and consequential on the country’s image in the eyes of the world.

    For a country often alleged for its double standards on global affairs, Trump’s stand on GERD adds up to the distrust of America. That, by and large, interpreted into eroding the influence border of USA.

    This way, Trump can not keep America Great Again!

    Let me say it again, I think Trump is confused with paralleling the poor material state of Ethiopians with their immeasurable moral sense and determination to their freedom & sovereignty of their country.


  • SADLY, DONALD J. TRUMP IS UNAWARE OF ETHIOPIA AND ITS PEOPLE!

    HABTAMU GIRMA
    MARCH 4, 2020
    JIGJIGA, ETHIOPIA



    When I think of Donald J. Trump, I see a well built institutional system in USA. Had it been to his zeal, the world would have burnt out. But, the Americans devised a sophisticated system to limit the ego of their leaders and statesmen.

    Not to mention the check and balance scheme among the three arms of a state, the American legislation allows even to limit the presidential decree. The recent senate decree to limiting the presidential powers of Trump on Iranian affairs is a recent showcase in this regard.

    By any standard, Trump’s leadership personality don’t fit the mighty of USA. We can mention countless cases and events on that. Luckily, whatever he speaks does not mean implemented, thanks to the American system of governance. However, that do not bring an excuse for his second term in office.

    Trump’s Gesture tells about him

    From the outset, Trump has shown the American people as a leader not to get proud on, but ashamed of. I remember words from an American researcher I met in Jigjiga couple of years back. He told me that every morning he woke up from his bed, he was contemplating what new fault this face of America (Trump) would make on the day in disgrace of him as an American citizen. I would say many Americans feel same about their leader.

    Trump in his Oval Office hosting Negotiating Parties on Nile River

    The thing Trump is doing against Ethiopian interest is nothing but a reflection of his absurd personality. Trump is unaware of this great Ethiopian nation and its people. I think Trump confused with paralleling the poor material state of Ethiopians with their immeasurable moral sense and determination to their freedom & sovereignty of their country. My message to him is to grow up!


    FOLLOW THIS LINK ABOUT MY TAKE ON TRUMP POLICIES, WHICH I DEPICT SOME 4 YEARS AGO!


    https://allafrica.com/stories/201708220779.html

  • ዛሬ ኢትዮጵያ  የውጭ ጠላት የላትም፤ የውስጥ እንጂ!

    ክብር እና ሞገስ ለዓድዋ ለሰማዕታት!


    ሀብታሙ ግርማ
    የካቲት 23 ቀን 2012 ዓ.ም
    ጅግጅጋ፣ኢትዮጵያ


    ዳግማዊ አጤ ምኒልክ፣ ንጉሰ ነገስት ዘ ኢትዮጵያ፤ የካቲት 23 1888 ዓ.ም ለኢትዮጵያዊያን ያሰሙት የድል ብስራት ይህ ነበር፦
    “….የምስራች! በእግዚአብሄር ቸርነት የየካቲት ቅዱስ ጊዮርጊስ ዕለት ጣሊያንን ድል አድርጌ መታሁት። በጨረቃ ሲገሰግስ አድሮ እሰፈሬ ድረስ መጥቶ ገጠመኝ። አምላክ ኃያላን ረድቶኝ ፈጀሁት፤ ደስ ብሎኛል ደስ ይበልህ”


    አባቶቻችን ከ124 ዓመታት በፊት የኢጣሊያ ወራሪ ሀይልን ድል የነሱት ከራሳቸው በፊት አገር አስቀድመው መስዋዕት መሆን መርሃቸው ስለነበር ነው።

    የወቅቱ የሀገሬ ትውልድ መርሁ ከራስ በላይ ንፋስ ሆኖ የበዛ ራስ ወዳድነት የአገር አንድነት እና ሉዓላዊነትን ለአደጋ ያጋለጠ የዘመናችን ጠላት ሆኗል፤ ዛሬ የራሳችን ጠላት ራሳችን ሆነናል!

    በመሆኑም የአድዋ ድልን ስንዘክር፦
    *ራሳችንን ለማሸነፍ ቃል የምንገባበት፣
    *ነገ የዛሬ መስዋዕትነት ውጤት መሆኑን የምንገነዘብበት፣ *ምክንያታዊነትን ገዢ መርህ የምናደርግበት፣

    እንዲሆን እመኛለሁ!

    ክብር እና ሞገስ ለሰማዕታት!

  • የምርጫ ቅስቀሳው ወደ ጸብ ቅስቀሳ እንዳይቀየር እንጠንቀቅ!

    ሀብታሙ ግርማ
    የካቲት 13 ቀን 2012 ዓ.ም
    ጅግጅጋ፣ኢትዮጵያ


    የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ፓርቲዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ የሚጀምሩበት ወቅት ባለፈው ሳምንት ይፋ ሆኗል። አሁን ባለው የአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጠብ እንደማንሳት ቀላል ነገር የለምና የምረጡኝ ቅስቀሳው ወቅት ደንበኛ የጠብ ወቅት ሊሆን የሚችልበት እድሉ ሰፊ ነው።

    ነገሩን አሳሳቢ የሚያደርገው ደግሞ ማህበረሰባችን የአመራር ቀውስ በገጠመው በዚህ ወቅት የምርጫ ቅስቀሳ ሊከወን መሆኑ ነው። ዛሬ በኢትዮጵያ ጠብን የሚያሟሙቅ እንጂ የሚያበርድ መሪ ወይም አስታራቂ ሽማግሌ ማግኘት ከባድ ነውና መራጩ ህዝብ የጠብ መንገዶችን መዝጋት ይገባዋል። ይህም ሲባል የምርጫ ቅስቀሳ መድረኮችን ከመደገፍ አንጻር እንጂ ከመቃወም አንጻር ማየት የለበትም ለማለት ነው።

    ለምሳሌ ኢዜማ በሚጠራው የድጋፍ ሰልፍ ላይ የአብን ወይም የኦነግ ደጋፊ በሰልፉ መገኘቱ ለምን ይሆናል?
    ኦነግ በሚጠራው የአደባባይ ምረጡኝ ቅስቀሳ የብልጽግና ፖርቲ ደጋፊ ምን ይሰራል?

    ስለዚህ ለሚቀጥሉት አራት ወራት የወጣው ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ለስድብ ወይም ቧልት፣ ከፍ ሲልም ለብሽሽቅ እና ጠብ አጫሪነት ሳይሆን ለስልጡን ዲሞክራሲያዊነት መጠቀም ያሻል። የምረጡኝ ዘመቻ ወቅቱን የምንደግፈውን ፓርቲ ፕሮግራሞችን ለመገምገም እንጂ ለብሽሽቅ መጠቀም የለብንም።

  • ከአምስቱ የፋሺስት ወረራ ዓመታት ምን እንማራለን?


    ሀብታሙ ግርማ ደምሴ

    ማስታወሻ፡-
    ይህ መጣጥፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአንባቢ የደረሰው ሚያዚያ 27 2008 ዓ.ም (እ.ኤ.አ ሜይ 7 ቀን 2016) ታትሞ ለንባብ በበቃው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ነበር፡፡ መጣጥፉን እንደገና ለአንባቢ የማድረሱ ፋይዳ የመጣጥፉ ጭብጥ ዛሬም ጉዳይ ስለሆነ ሲሆን፤ በዋናነትም ዘንድሮ 71ኛውን ዓመት የነጻነት በዓላችንን በምናከብርበት ወቅት ከዚያ ታሪክ ምን ያህል ተምረናል የሚለውን አንገብጋቢ ጉዳይ በአንባቢ አእምሮ ለማጠየቅ ነው፡፡
    ሰናይ ንባብ!

    በአዲስ አበባ ከተማ አራት ኪሎ አደባባይ በክብር የቆመው ሐውልት የኢትዮጵያዊያን የነጻነትና ተጋድሎ አርማ ነው።

    አምስቱ የፋሽስት ወረራ አመታት (1936-1941 ዓ.ም)

    ከ1920ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ የዘለቀው የፋሺስት ኢጣሊያ ጦር፣ አንዳንድ የጠረፍ አካባቢዎችን ከመቆጣጠር አልፎ ቀስ በቀስ እግሩን እያሰፋ መላ አገሪቱን በእጁ ለማስገባት መንቀሳቀሱን ተከትሎ የአገር ህልውና አደጋ ላይ ወደቀ:: የፋሺስት ትምክህት አይሎ ከሃምሳ ዓመታት በፊት በዓድዋ የጦር አውድማ የደረሰበትን ሽንፈት ለመበቀል ጦሩን አደራጅቶ በማይጨው መሸገ:: የማይጨው ጦርነት ውጤት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚያረጋግጥ ወይም የኢጣሊያን ቅኝ ገዢነት የሚያውጅ ነበር፡፡

    የኢትዮጵያ አርበኞች ወደ ማይጨው የጦር አውድማ በጉዞ ላይ

    በጦርነቱ ዘመናዊ መሳሪያ ታጥቆ የነበረው የኢጣሊያ ሰራዊት የበላይነት ያዘ፥ የወገን ጦርም አፈገፈገ:: የጦሩ ጠቅላይ አዛዥ የነበሩት ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ኮረም ላይ ጦሩን አሰባስበው ወደ ውጊያ ተመልሰው ለመግባት ባሰቡ ጊዜ የንጉሱ የቅርብ ሰዎችና የጦር አበጋዞቻቸው በዚህ የንጉሱ ወሳኔ ለሁለት ተከፈሉ፤ ንጉሱ በአገር ቤት ሆነው ጀግኖች አርበኞችን እያስተባበሩ፣ የኢጣሊያንን ጦር በዱር በገደሉ መጋፈጥ አለባቸው የሚሉ መኳንንትና መሳፍንት የሚኖራቸውን ያህል፣የለም የግርማዊነታቸው ኮረም ላይ መዋጋትና መሞት ጠላትን ከመጥቀም በቀር ፋይዳ የለውም ብለው የተከራከሩም ነበሩ::
    ኢትዮጵያዊው የታሪክ ባላባት ተክለ ጻዲቅ መኩሪያ “ከአጼ ቴዎድሮስ እስከ ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ” በሚለው መጽሀፋቸው እንዳሰፈሩት፤ንጉስ ነገስቱ በጉዳዩ ላይ የሚኒስትሮች ምክር ቤት እንዲወስን ጠይቀው፣በዚህም ድምጸ ውሳኔ ተካሂዶ፣ ምክር ቤቱ ሃያ አንድ ለሶስት በሆነ ድምጽ ንጉሰ ነገስቱ አገር ለቀው እንዲወጡ ወሰነ፡፡ ከዚህ በኋላ ግርማዊ ንጉሰ ነገስት፤‘የኔ ወደ አዲስ አበባ መመለስ ለህይወቴ መሳሳት ሳይሆን ለኢትዮጵያና ለህዝቦቿ ጠቀሜታ ያደረጋችሁት መሆኑን ቃል ግቡልኝ’ ብለው ጳጳሱ ከገቡላቸው በኋላ እንግዲያውስ የተረፈውም ጦር እንዲመለስ ንገሩ ብለው ከተሰበሰበ በኋላ ደጀን እየሆኑ ጉዞ ወደ አዲስ አበባ ጀምረው፣ ሚያዚያ 3 ቀን 1936 (እ.ኤ.አ) ከኢትዮጵያ ተነስተው ከተወሰነ ቀን በኋላ ወደ ጄኔቭ አመሩ::

    እ.ኤ.አ ማርች 31 ቀን 1936 ዓ.ም ቀዳማዊ ሀይለስላሴ በማይጨው የጦር አውድማ ጸረ-አውሮፕላን ከባድ መሳሪያ በመተኮስ ላይ (ምንጭ፡- http://ww2db.com)


    የአዲስ አበባ መያዝ አይቀሬ ነበርና የንጉሰ ነገስቱ መቀመጫን መቀየር ያስፈልግ ነበር፤ እናም የት ይሁን በሚለው ጉዳይ ላይ የተለያዩ አስተያየቶች ቢመጡም የብላቴን ጌታ ሎሬንዞ ታዕዛዝን ያህል ግን ሚዛን የሚደፉ አልነበሩም፡፡ ሎሬንዞ ታዕዛዝ የመንግስቱ መቀመጫ እንዲሆን ብለው ያጯት ጎሬ ነበረች፡፡ የሎሬንዞ ታዕዛዝ ተቀባይነት በማግኘቱ ቀዳማዊ አጼ ሀይለስላሴ የመንግስታቸውን መቀመጫ ወደ ጎሬ አንዲዞር፣ የዘውዳዊውን መንግስት እንዲጠብቁ ደግሞ ልዑል ራስ እምሩ ሀይለ ስላሴን ሰይመው፣ አዲስ አበባን ለቀው በባቡር ወደ ጅቡቲ፣ ከዚያም በመርከብ ተሳፍረው ወደ አውሮፓ ተጓዙ፡፡

    ራስ እምሩ ሀይለስላሴ


    በማርሻል ግራዚያኒ የተመራው የፋሽስት ኢጣሊያ ጦርም ሚያዚያ 27 ቀን 1927 ዓ.ም አዲስ አበባን ተቆጣጠረ፡፡ጠላት አዲስ አበባ ከተማ ከመድረሱ ኢትዮጵያዊያን ከባህላቸውና ማንነታቸው እንዲፋቱ ለማድረግ ያለሙ ተግባራትን በዘመቻ መልክ ፈጸመ:: ፋሺስት ያደረገው የመጀመሪያው ተግባር ታሪኩን መበረዝና የሀሰት ታሪክን መፈብረክ ነበር፣ የኢትዮጵያዊያንን ታሪክ ለማውደም የተጠቀመበት ስትራቴጂ ደግሞ ኢትዮጵያዊያን ምሁራንንና ታላላቅ ጸሀፍትን ከያሉበት እያደነ ማሰር፣ መግደልና በአማርኛና በግዕዝ የተጻፉ መጻህፍትን በዘመቻ ማቃጠል ነው፡፡
    ፋሺስት የባህላዊውን ትምህርት እንዲቆም በማድረግ፣ራሱ አስኳላ በሚል የሰየማቸውን ትምህርት ቤቶች በመላው ኢትዮጵያ በማቋቋም፣ የትምህርት ስርዓቱ የራሱን ፕሮፓጋንዳና አጀንዳ ማስፈጸሚያ መሳሪያ ለማድረግ ሞከሯል:: ወራሪው የፋሺስት ሀይል በማይጨው የጦር አውድማ ድል ቢቀናውም፣ ተረጋግቶ ኢትዮጵያውያንን ለመግዛት ግን አልተቻለውም::ኢትዮጵያዊያን ለአገራቸው ነጻነት ሲሉ ከዳር እስከ ዳር አንድ ሆነዉ በመነሳት በዲፕሎማሲውና በጦር ግንባር የሞት ሽረት ትግል አድርገዋል::

    በኢትዮጵያ የኢጣሊያ ጦር አዝማች ማርሻል ሮዶልፎ ግራዚያኒ

    የአርበኞች ትግል

    ጀግኖች አርበኞች በገጠርና በከተማ፣ በአገር ቤትና በውጭም ሆነው በተለያዩ የጦር አበጋዞች ተደራጅተው ፋሺስትን ፋታ አልሰጡትም ነበር:: ለአገራቸው ሉዓላዊነት ቀናኢነት የነበራቸው ጀግኖቻችን ህዝቡን እያስተባበሩ በፋሺስት ላይ እንዲነሳ አድርገዋል፣ ትግሉንም መርተዋል:: ከእነዚህም መካከል ራስ ዕምሩ ሀይለ ስላሴ፣ ደጃዘማች ከበደ ተሰማ፣ራስ ደስታ ዳምጠው፣ ከበደች ስዩም፣ በላይ ዘለቀ፣ የሰላሌው ታዳጊ አቢቹ፣ ሀዲስ አለማየሁ፣ ስንዱ ገብሩ፣ ወዘተ… ለአብነት መጥቀስ ይበቃል::

    ታላቁ አርበኛ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጴጥሮስ

    በከተሞችም እንዲሁ ትግሉን ያፋፋሙ አርበኞች በርካታ ናቸው፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ የአብረሃም ደቦጭና ሞገስ አስገዶም ገድል፣ የአቡነ ጴጥሮስ ሰማዕትነት፥ በፋሺስት መናገሻ ሮም ከተማ የአብዲሳ አጋ ጀግንነት አለምን አጃኢብ ያሰኙ ነበሩ:: ወራሪው የኢጣሊ0ያ ሀይል አርበኞቹን በኢትዮጵያ የቄሳርን ገዢነት አምነው ከተቀበሉ ከእስር እንደሚፈታቸው፣ዳጎስ ያለ ጉርሻን እነሆ ቢላቸውም ፈጽሞ አሻፈረኝ በማለት፣አገርን በምንም መለወጥ እንደማይቻል፣ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ምን ማለት እንደሆነ ፋሺስት እንዲገነዘብ አድርገዋል::

    በዲፕሎማሲው ዘርፍ የተደረጉ ጥረቶች

    የፋሺስትን ሀይል በጦር ማሸነፍ አልሆነምና ሌላ የትግል ስልት መፈለግ የግድ ነበር፤ከእነዚህም አንዱ ፋሺስትን በዲፕሎማሲው ግንባር መግጠም ነበር፡፡ በኢኮኖሚና ወታደራዊ መስክ እጅጉን ኋላ ቀር የነበረችው ኢትዮጵያ፤ በአለም አቀፍ መድረኮች ከፍጸኛ ተጽዕኖ ፈጣሪ የነበረችውን ሃያሏን ኢጣሊያን በዲፕሎማሲው ግንባር ለመፋለም ስትነሳ ‘በየትኛው አቅሟ ብለው የተሳለቁ ብዙዎች ቢሆኑም ይህን ፉርሽ ያደረጉ የዲፕሎማሲ ጀግኖች አሉን፡፡
    በአምስቱ የፋሺስት ወረራ ዓመታት ወቅት የንጉሰ ነገስቱ ተወካይ ሆነው የተለያዩ አገራት እየተዘዋወሩ ጉዳይ አስፈጽመዋል፤ የኢትዮጵያን በደልና ብሶት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በማሳወቅ ወራሪውን የፋሺስት መንግስት የዲፕሎማሲ ጫና ስር እንዲወድቅ ብዙ ሰርተዋል፡፡ በዚህ ረገድ ራስ ቢትወደድ መኮንን እንዳልካቸው፣ ብላቴን ጌታ ህሩይ ወልደ ስላሴ፣ ብላቴን ጌታ ሎሬንዞ ታዕዛዝ ተጠቃሽ ናቸው::

    የአምስቱ ዓመታት የፋሺስት ወረራ ምን አጎደለብን?

    የፋሺስት ወረራ በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ላይ ያደረሰው ሰብዓዊ፣ ቁሳዊና መንፈሳዊ ሀብት ውድመት ከባድ ነበር:: በአምስቱ ዓመታት ብዙ ሺህ ኢትዮጵያዊያን አርበኞች ሞተዋል፥ ቆስለዋል::

    ተሾመ ዋጋው የተባሉ ምሁር፤ ‘Education in Ethiopia: Prospect and Retrospect’ በሚል እ.ኤ.አ በ1979 ዓ.ም ባሳተሙት የምርምር ስራቸው እንዳሰፈሩት፤ ከ1928 እስከ 1933 ዓ.ም በዘለቀው ወረራ ኢትዮጵያ ሰባ አምስት በመቶ (75%) የሚሆኑትን የተማሩ ዜጎቿን አጥታለች፡፡

    ወረራው ጥሎት ያለፈው ማህበራዊ ስንክሳርም ቀላል አይደለም::

    ደራሲ አሰፋ ገብረ ማርያም ‹እንደወጣች ቀረች› በተሰኘው የስነ ጽሁፍ ስራው፤የፋሺስት ወረራ የዝሙት አዳሪነት፣የትምባሆ ሱስ እንዲስፋፋ ስለማድረጉ ጽፏል::

    ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም “አዳፍኔ: ፍርሃትና መክሸፍ” በተሰኘው መጽሃፋቸው እንዳሰፈሩት፤የፋሺስት ወረራ የኢትዮጵያን አንድነትን የሸረሸረ ነበር፡: ተጽዕኖውም ዛሬም ከ75 ዓመታት በኋላ ይታያል:: ምንም እንኳን ኢትዮጵያ በቁሳዊ ሀብትና ኋላ የቀረች ቢሆንም ለውጭ ወራሪዎች እጅ ሳትሰጥና ህልውናዋ ሳይከሽፍ የቆየበት ምክንያቱ የመንፈሳዊው ስልጣኔ መገለጫ የሆኑትና ለዘመናት የኢትዮጵያ ህዝብ ንብረት ሆነው በኖሩት እሴቶች ማለትም አርቆ አሳቢነት፣ ሀይማኖተኝነትና ፈሪሃ እግዚአብሄር፣ መልካም ስነ ምግባር፣ መንፈሰ ጠንካራነት፣ ለክብርና ኩራት ቅድሚያ መስጠት፣ ለአገር ነጻነትና ሉዓላዊነት መስዋዕትነት ተጋድሎ ማድረግ ወዘተ…. ናቸው፡፡ ታዲያ ይህ መንፈሳዊ ስልጣኔ እስከ መጨረሻው የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ አልተቻለውም፡፡

    ብልህ ከሁለት ይማራል፣ አንድም ከፊደል ሀ ብሎ፣ አንድም ከመከራ ዋ ብሎ

    የአምስቱ ዓመታት ወረራ የኢትዮጵያ ስልጣኔ እሴቶችን ያመነመነ ነው:: የኢትዮጵያ ሉአላዊነት መሰረት የሆኑት እነዚህ እሴቶች መሸርሸር ደግሞ የአገር አንድነት አደጋ ላይ እንዲወድቅ አድርጓል:: ብልህ ከሁለት ይማራል፣ አንድም ከፊደል ሀ ብሎ፣ አንድም ከመከራ ዋ ብሎ እንዲሉ፤ ከአምስቱ የመከራ ዓመታት ምን ትምህርት አገኘን የሚለው ወሳኝ ጉዳይ ይመስለኛል::

    በመሰረቱ የፋሺስት ወረራ የተሳካው በውስጥ ድክመታችን የተነሳ ነው፡፡ እንደ ህዝብ፣ እንደ መንግስት የምንወስደው ሃላፊነት አለብን:: ኢትዮጵያዊያን ለዘመናት የኖርነው የህይወት ዘይቤና ፍልስፍና ስራን የሚያበረታታ አለመሆኑና ህዝቡ ለቁሳዊ ሀብት ያለው ግምት ዝቅተኛ መሆን ኢትዮጵያን ከሌላው ዓለም በኢኮኖሚ በእጅጉ ወደ ኋላ አስቀርቷታል፡፡ በእርግጥ በተለያዩ የዘመን ማዕቀፎች ኢትዮጵያን ያስተዳደሩ አብዛኞቹ መሪዎች ህዝቡ ይህን አስተሳሰብ እንዲያዳብር አይፈልጉ እንደነበር ተደጋግሞ ቢጻፍም ህዝቡ ከተወቃሽነት አይድንም፥ መሪዎች ህዝቡን መስላሉ የሚለውን መርሳት የለብንም::
    የሆነው ሆኖ የኢጣሊያ ጦር ዘመናዊ መሳሪያ ታጥቆ፣ በምድርና በአየር በወገን ጦር ላይ መዓቱን ሲያወርድ፣ኢትዮጵያዊያን አርበኞች ግን ከሃምሳ አመታት ቀደም ብሎ በአድዋ ጦርነት ታጥቀው የዘመቱትን ባህላዊ መሳሪያዎች ነበር የታጠቁት፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን እንዲህ ጽፈዋል፡-

    ‘………ኢትዮጵያ ያለችበትን በጣም ዝቅተኛና ቆሞ ቀር ደረጃ በተግባር አስመሰከረች፤ይህ አዲስ ዕውነት የኢትዮጵያ ህዝብ ለዘመናት የነበረውን አልበገር ባይነት ከነኩራቱና ክብሩ ገፈፈው፤ የመንፈስ ሃይሉ ደቀቀ፤ አንገቱን ደፋ፡፡ (ከ“አዳፍኔ: ፍርሃትና መክሸፍ”፣ገጽ 133 ላይ የተወሰደ)

    ለማይጨው ጦርነት መሸነፍ ሌላው ሰበብ፣ ጦሩን ያዘመቱና የመሩ ሹማምንት ከልባቸው አልነበሩም፣ ወኔ የከዳቸው ነበሩ የሚሉ መረጃዎች አሉ:: የዚህ ምክንያት ደግሞ የዘመኑ የኢትዮጵያ ፖለቲካና የአስተዳደር ስርዓት ለአገራዊ መግባባት በዝቅተኛ ደረጃ እንኳ እውቅና ያልሰጠ፣ ፍትህና መልካም አስተዳደር የማያውቅ፣ ደካማ መሆኑ ነበር::
    የአሁኑ የኢትዮጵያ ገዢዎች ከዚህ መማር ያለባቸው ቁም ነገር ቢኖር፣ የሚከተሉትን የፖለቲካ ስርዓት መለስ ብለው መቃኘት እንደሚገባቸው ነው:: አስተዳደራቸውና ፖሊሲዎቻቸው በተለያየ ደረጃና ስልጣን ያሉ የመንግስት አካላትን የማይከፋፍል፣ የህዝብና መንግስትን ግንኙነት የማያሻክር መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋቸዋል::
    ይህ ካልሆነ ግን ውስጣችንን አድክሞ የኢትዮጵያና ህዝቦቿን ሰላምና ብልጽግናን ለማይሹ የውጭ ሀይሎች ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፥ የአገርና የህዝብ ህልውናም በእጅጉ አደጋ ላይ እንደሚወድቅ፣ ለራሳቸው ለፖለቲካው አራማጆችና (ገዥዎች) ጭምር የማይበጅ መሆኑን ከአጼ ሀይለ ስላሴና ባለሟሎቻቸው ስደትና የመንግስታቸው መፍረስ ሊማሩ ይገባል::

    በመጨረሻም በየዓመቱ የየካቲት 12 ሰማዕታት ቀንን ስናከብር በደረሰብን ሰቆቃና ጥፋት እየተቆጨን ሳይሆን ውስጣችንን (ራሳችንን) እየመረመርን፣ ስህተቶቻችንን ነቅሰን ዳግም እንዳንሳሳት በምንጠነቀቅበት አግባብ መሆን አለበት እላለሁ:: መልካም የድል በዓል ለሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብና የኢትዮጵያ ወዳጆች ሁሉ ይሁን!! ክብር ለጀግኖች አርበኞቻችን!!

  • የሙስሊም ወገኖቻችን ጉዳይ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጉዳይ ነው!

    ሀብታሙ ግርማ (በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ረዳት ፕሮፌሰር)
    ጥር 25 ቀን 2012 ዓ.ም
    ጅግጅጋ፣ ኢትዮጵያ


    መግቢያ



    ጉዳዩን ፖለቲካዊ ካላደረግነው በቀር ለሞጣ ሙሰሊሞች መቆም ያለበት አማራው ወይም ሙስሊሙ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ብቻ አይደለም፤ ሰው የሆነ ሁሉ በሰብዓዊነት ከጎናቸው ሊቆም ይገባል። ከዚህ አኳያ በግሌ ማድረግ ያለብኝን የሰብዓዊነት የሞራል ግዴታ ለመወጣት ለተጎዱት ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ዛሬ የአቅሜን ለግሻለሁ።

    የዚህ መጣጥፍ ዓላማ የሞጣ ሙስሊሞችን ጉዳት ከሰብዓዊነት ይልቅ ፖለቲካዊ መልክ ለመስጠት የመሞከር የተሳሳተ አዝማሚያ በምክንያት ለመሞገት ነው። በዚያውም የሙስሊሙ ማህበር ጥያቄዎችን ፍትሃዊነት ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ሁነቶች አንጻር መገምገም ነው።

    የተንሸዋረረው የታሪክ ትንተና እና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ስንክሳሮች


    ካለፈው ግማሽ ክፍለ ዘመን ወዲህ የኢትዮጵያ የፖለቲካ አሰላለፎች የትግል መሰረት የማርክሲስታዊ የታሪክ ትንተና መሣሪያ የሆነው የጨቋኝ- ተጨቋኝ ክፍፍል (exploiter-exploited dictum) ነው።

    በ1960ዎቹ የነበሩ የፖለቲካ ሃይሎች አጀንዳ መሰረት ይህ ማርክሲስታዊ የቅራኔ የታሪክ ሆኖ የቅራኔው መሰረት ላይ ሁለት አተያይ ነበር። አንደኛው የፖለቲካ ቡድን የኢትዮጵያን ታሪክ የሚተነትነው በመደባዊ ቅራኔ ሲሆን፣ ሁለተኛው የፖለቲካ ሀይል የኢትዮጵያ ታሪክ ከብሔር ቅራኔ አንጻር ነበር። የኋለኛው ቡድን ዛሬም በተጽዕኖው የኢትዮጵያን ፖለቲካ እያሾረው ይገኛል። ብሔር ተኮር የጨቋኝ-ተጨቋኝ ትርክት ዋናው የፖለቲካ ስንቅ ሆኖ ዛሬም እየዘወረን አለ።

    ነገር ግን በእኔ ዕውቀት የትኛውም አይነት ቅራኔን መሰረት ያደረገ የታሪክ ትንተና የፖለቲካ ጥሬ ዕቃ ማድረጉና ፖለቲካን ለመከወን የሚደረግ ጥረት ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል። ጥቅሙ ታሪካዊ ቅራኔን በማለዘብ ለዘላቂ የማህበረሰብ አንድነት እና የተሳካ ብሔረ መንግስት ግንባታ አስተዋጽኦ አለው። አሉታዊ ገጽታው የፖለቲካ ሥርዓቱ ጊዜው የሚጠይቀውን የህዝብ ችግር ለመፍቻ ከመሆን ይልቅ ተጨማሪ ትውልድ ተሻጋሪ ቅራኔዎችን ለመፍጠር በር ከፋች ሊሆን የሚችልበት እድል ያሰፋዋል።
    ቅራኔን መሰረቱ ባደረገ የፖለቲካ ስሪት ፖለቲካ ቂም መወጫ መሳሪያ ስላለመሆኑ ዋስትና ሊኖር አይችልም፡፡ ይህም የቀድሞው ጨቋኝ የዛሬ ተጨቋኝ፤ የዛሬ ተጨቋኝ ደግሞ በተራው የነገ ጨቋኝ የመሆኑ ጉዳይ አይቀሬ ያደርገዋል፡፡ በመሆኑም የፖለቲካው ስርዓት በጭቆና አዙሪት ተመልቶ ፖለቲካ የችግር መፍቻ ቁልፍ ሳይሆን የችግር ምንጭ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ ኢትዮጵያን የገጠማት የፖለቲካ ቀውስ መሰረታዊ መነሻውም በቅራኔ ታሪክ የተገነባው የፖለቲካ ስርዓት ነው የሚል ዕምነት አለኝ፡፡

    የሆነው ሆኖ የቅራኔ ታሪክን መሰረቱ ያደረገው የኢትዮጵያ ፖለቲካ የተንሸዋረረ መሆኑ ሳያንስ የታሪካዊ ቅራኔውን በትክክለኛ አስረጅነት አለመግለጹ ሌላው ችግር ነው፡፡ ከዚህ አንጻር የብሔር ቅራኔን መሰረቱ ያደረገው የፖለቲካዊ ስርዓት የኢትዮጵያን ህዝብ የዘመናት ችግር ከመግለጽ አንጻር ቢያንስ ምሉዕነት የጎደለው ነው፡፡

    የዚህ ችግር ነጸብራቅ ከሆኑ አንዱ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ለዓመታት ሲያነሳቸው ለነበሩ ጥያቄዎች የፖለቲካ ስርዓቱ መልስ ከመስጠት ይልቅ ጥያቄውን የመጠርጠር አዝማሚያ የነበረው መሆኑ ነው፡፡

    የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጥያቄ ታሪካዊ ዳራ


    ብሔር ተኮር የጭቆና የታሪክ ትርክት ካልመለሳቸው ጉዳዮች አንዱ የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን ጉዳይ ነው።የፖለቲካን አጀንዳ ከታሪክ ቅራኔ አንጻር እንኳ ቢቃኝ የኢትዮጵያ የታሪክ ትንተና መሆን የነበረበት ብሔራዊ ቅራኔ ሳይሆን በመደባዊ ቅራኔ ነበር።

    የረጅም ዘመን የኢትዮጵያ የሥነ መንግስት ታሪክ የፊውዳል ሥርዓተ ማህበር ነው። የፊውዳል ሥርዓተ መንግስት አሻራዎች አንዱ የሚና እና የተጠቃሚነት ክፍፍል ማህበረሰባዊ መሰረትን ያማከለ ነበር። ማህበረሰባዊ መሰረቱ ሀይማኖት፣ ጾታ፣ ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ደረጃ (የባላባት ማህበረሰብ፣ የጭሰኛ ማህበረሰብ፣ የቀጥቃጭ ማህበረሰብ፣ የአዝማሪ ማህበረሰብ ወዘተ….) ሊሆን ይችላል። በዚህም የፖለቲካው፣ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ ወዘተ ሚና፣ ደረጃ ወይም ተጠቃሚነት ማህበረሰባዊ ማንነትን መሰረት ያደረገ ነበር።

    በሀይማኖት ደረጃ የማህበረሰቦችን ክፍፍል ካየን ሙስለሙ የማህበረሰብ ክፍል ኢኮኖሚያዊ ሚና ንግድ ነበር። የክርስቲያኑ ማህበረሰብ ሚና ኢና ተጠቃሚነት ደግሞ በፖለቲካ፣ በቢሮክራሲ፣ በትምህርት፣ በግብርናው እና በመሬት ባለቤትነት ዘርፎች ላይ ነበር። በመሆኑም የሙስሊሙ ማህበረሰብ በፖለቲካ እና በመንግስት አስተዳደር ውስጥ ሚናው ከሞላ ጎደል ምንም ነበር። ይህን ታሪካዊ ሀቅ መካድ አይቻልም።

    ዛሬ የፖለቲካና የህዝብ አስተዳደር አካታች ይሁን ተብሎ ጥሩ ሂደት ላይ እንገኛለን፤ ይህ የአካታችነት መርህ አንደኛው አስረጅ በታሪክ አጋጣሚ በፖለቲካና በመንግስት ሚናቸው አናሳ የነበሩ የማህበረሰብ ክፍሎች (ለምሳሌ ሴቶች፣ ሙስሊም ማህበረሰብ አካላት፣ ወዘተ..) ወደ ቢሮክራሲው እና የመንግስት ስራ አስፈጻሚ አካላት ማምጣት ነው፡፡ በመንግስት ቢሮክራሲ እና የፖለቲካ ሚና መጨመር አለበት የሚለው የሙስሊም ወንድሞቻችን ጥያቄ ፍትሃዊነት ከዚህ ነባራዊ የኢትዮጵያ ታሪክ አንጻር ብንመለከተው ሚዛናዊ ፍርድ እንዲኖረን ያደርጋል።

    ከዚህ አንጻር ሙስሊም ወገኖች ተወካዮች የመንግስት የአስተዳደራዊ ውክልና ሲጠይቁ የግብጽ እና የሌሎች የአረብ አገራት ተላላኪ አድርጎ መውሰድ ፍረጃ አንጂ እውነትን መሰረት ያደረገ አይደለም። በመሠረቱ በአገር ላይ የሚኖር ስጋት የለም ማለት አይቻልም፤ ነገር ግን ይህ የመንግስት የደህንነት መዋቅር ሥራ ነውና ለሚመለከተው አካል ብንተወው ጥሩ ይመስለኛል።

  • የሁለት ወረርሽኞች ወግ፡ የኮሮና ወረርሽኝ እና ስፓኒሽ ፍሉ (የሕዳር በሽታ)

    THE TALE OF TWO DISEASES : Corona Virus Vs Spanish Flu


    ሀብታሙ ግርማ ደምሴ

    እንደ መግቢያ

    ሰሞነኛ የአለማችን መነጋገሪያ የኮሮና ወረርሽኝ ነው፡፡ በሽታው ከአገረ ቻይና መነሻውን አድርጎ በፍጥነት ወደ ሌሎች አገራት እየተዛመተ ነው፡፡ የአለም የጤና ድርጅት የበሽታው ስጋት ደረጃ የአለማቀፍ ወረርሽ መሆኑን ጥር 20 ቀን 2012 ዓ.ም አውጇል፡፡
    በ ‘የሁለት ወረርሽኞች ወግ ‘ መጣጥፌ በስፓኒሽ ፍሉ ወይም የህዳር በሽታ እና የኮሮና ወረርሽኞችን ዝምድና በመፈተሽ ከተሳካልኝ አንባቢን አንድ ክፍለ ዘመን ወደ ኋላ እጎትታለሁ፤ የጽሁፌ ዓላማ በአንባቢ አእምሮ ውስጥ የዘመን ግጥምጥሞሽ ትዝብት አልያም ‘ታሪክ ራሱን ይደግማል‘ የሚለው ብሂል ለመጫር የሚደረግ (የሚሳካ አልያም የከንቱ) ሙከራ ነው፡፡

    ማስታወሻ፦ ከመጠነኛ ማሻሻያ በቀር ይህ መጣጥፍ በህዳር 2008 ዓ.ም በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ለንባብ የበቃ ነው።

    የኮሮና ወረርሽኝ እና ስፓኒሽ ፍሉ ዝምድና ይኖራቸው ይሆን?

    በእኔ አተያይ ስፓኒሽ ፍሉ (የህዳር በሽታ) እና የኮሮና ወረርሽኞች በብዙ መልኩ ተመሳስሎሽ አላቸው፡፡ የተመሳስሎሻቸው መገለጫዎች ከብዙ በጥቂቱ፡-
    • የበሽታዎቹ አማጪ ተህዋስ ቫይረስ ነው፤
    • ሁለቱም የመተንፈሻ አካላትን የሚያጠቁ ናቸው፤
    • የበሽታው ምልክቶች እና በሽታው የሚተላለፍባቸው መንገዶች ተመሳሳይነት አላቸው
    • ሌላው የወረርሽኞቹ ተዛምዶ የጊዜ(የዘመን) ነው፡፡
    o ከዚህ አንጸር ሁለቱም በአለም የታዩት በጥር ወራት፣ በክፍለ ዘመኑ ሁለት አስርት አመታት መባቻ ነው፡፡
    o ታሪክ ራሱን ይደግማል እንደሚሉት አበው፣ የኮሮና ወረርሽኝ የተከሰተው የስፓኒሽ ፍሉ ወረርሽኝ ከተከሰተ መቶ ዓመታት (አንድ ክፍለ ዘመን) ሲደፍን መሆኑ ነው፡፡
    o ወረርሽኞቹ የተከሰቱባቸው ወቅቶች የዓለም የፖለቲካ እና የደህንነት አውድና ስሪት ተመሳስሎሽ አላቸው፡፡ ይህን ለማብራራት ያህል፡-
     የህዳር በሽታ የተከሰተው አለም በከፍተኛ የብሔርተኝነት ጡዘት የደረሰበት ነበር፤ የብሔርተኝነት ጡዘቱ ባመጣው ጣጣ የአለም ሃያላን አገራት የጦር መሳሪ እሽቅድምድም የገቡበት ነበር፤ ይህ የአለም ሃያላን እሰት እገባ በርትቶ በአለም ታሪክ የአንደኛው የአለም ጦርነት ወቅት ነበር፡፡ ዛሬም ሶስተኛው አለም ጦርነት አደጋ በአለም ያንዣበበበት ወቅት እንደሆነ እየኖርነው ጉዳይ ስለመሆኑ ማብራሪያ አያስፈልገውም፡፡

    የኮሮና ወረርሽኝን በተመለከተ አንባቢ ስለበሽታው ወቅታዊ መረጃ እንዲሁም ስለ ወቅቱ የአለም የፖለቲካ እና የደህንነት ትኩሳት መጠነኛ ግንዛቤ አለው የሚል እምነት አለኝ፡፡ ስለሆነም የሁለቱን ወረርሽኞችን ተዛምዶ ከላይ ባስቀመጥኩት የተመሳስሎሽ ነጥቦች ያወዳድር ዘንድ ስለ ስፓኒሽ ፍሉ (የህዳር በሽታ) ወፍ በረር ታሪካዊ ቅኝት አደርጋለሁ፡፡

    የኮሮና ቫይረስ ስርጭት አሃዛዊ መረጃዎች

    የስፓኒሽ ፍሉ (የህዳር በሽታ) ታሪካዊ ዳራ

    የ20ኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያ ሁለት አስርት ዓመታት ለመላው የዓለም ህዝብ የሰቆቃ ዓመታት ነበሩ፤ ምክንያቱ ደግሞ የወቅቱ ሃያላን መንግስታት በሁለት ጎራ ሆነው ጦርነት ውስጥ ገብተው ስለነበር ነው፡፡ እ.ኤ.አ ከ 1914 ዓ.ም እስከ 1918 ድረስ የዘለቀውና የ15 ሚሊዮን ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው ይህ ጦርነት በታሪክ የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ተብሎ የሚታወቀው ነው፡፡ የጦርነቱ ማብቃት ሊታወጅ ጥቂት ሲቀረውና ዕልቂቱ ቆመ ሲባል ግን የዓለም ህዝብ ሌላ ፍዳ ማስተናገድ ግድ ሆነበት፤ በሰው ሰራሽ ችግሮች (በዋነኝነት በጦርነት) ተወጥሮ የቆየው መላው የአለም ህዝብ አሁን ደግሞ በእንፍሉዊንዛ በሽታ ከዳር እስከ ዳር ተጠቃ፡፡:
    በተለምዶ የእሰፓኒሽ ፍሉ ተብሎ የሚታወቀው ይህ ወረርሽኝ መነሻው ከወደ አሜሪካ እንደሆነ ይታመናል፡፡ ይህም እ.ኤ.አ በጥር ወር 1918 ዓ.ም በአንደኛው የአለም ጦርነት ማብቂያ ዋዜማ በጦርነቱ ለመካፈል የአሜሪካ ወታደሮች ወደ አውሮፓ ለመጋዝ ዝግጅት በሚያደርጉበት ወቅት ከተከሰተው ወረርሽኝ ጋር ይያያዛል፡፡ በካንሳስ በሚገኘው ፉንስተን የወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል የተቀሰቀሰው ወረርሻኙ በሶስት ቀናት ብቻ 45 ሺህ የሚሆኑ ወታደሮችን አጠቃ፤ ወታደሮቹ አትላንቲክን አቃርጠው አውሮፓን እንደረገጡ በሸታውም አውሮፓ ደረሰ፡፡

    በካንሳስ በሚገኘው ፉንስተን የወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል በበሽታው የተጠቁ ወታደሮች በህክምና ላይ

    የእንፍሉዌንዛ በሸታው በአውሮፓ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው በፈረንሳይ ቢሆንም በጦርነቱ ምክንያት ፕሮፓጋንዳ መጠቀሚያ ይሆናል በሚል ወረርሽኙ ለህዝብ ሳይገለጽ ተደብቆ ቆይታል፡፡ በሽታው ይፋ የሆነው እ.ኤ.አ በህዳር ወር 1918 ዓ.ም በስፔን በሽታው ለመጀመሪያ ጊዜ መታየቱን ተከትሎ ነበር፡፡ ስፔን በጦርነቱ ተካፋይ አልነበረችምና በአገሪቱ የጦርነት ጊዜ ሳንሱር አልነበረም፤ በመሆኑም የበሽታው መስፋፋት ከፍተኛ የሚዲያ ሽፋን በማግኘቱ ወረርኙ እስፓኒሽ እንፍሉዌንዛ (ስፓኒሽ ፍሉ) የሚለውን ስያሜ አገኘ፡፡

    ስፓኒሽ ፍሉ (የህዳር በሽታ) መነሻ ምክንያት፣ ምልክቶች እና ስርጭቱ

    የስፓኒሽ ፍሉ አማጪ ቫይረስ ባለመታወቁ መድሃትም ሆነ ማስታገሻ አልተገኘለትም፤ የአማጭው ቫይረስ የታወቀው እ.ኤ.አ በ1933 ዓ.ም በእንግሊዛዊያን ሳይንቲስቶች ሲሆን፣ የበሽታው አማጪ ቫይረስ በሳይንሳዊው አጠራር H1N1 ተብሎ ይታወቃል፡፡ በዚህም በሽታው በተቀሰቀሰበት ወቅት በህክምና ስርጭቱን ለማቆም አስቸጋሪ አድርጎታል፡፡ በጥቂት ጊዜም ከአሜሪካ እስከ አውሮፓ፣ ከኤሺያ እስከ አፍሪካ፣ከአርክቲክ እስከ ፓስፊክ ደሴቶች ድረስ በከፍተኛ ፍጥነት ተዛመተ፡፡

    በሽታው እንዲዛመት የአለም የወቅቱ ነባራዊ ሁኔታ ምቹ ሁኔታን ፈጥሮ ነበር፤ ይህም ወታደሮች ከአንዱ የአለም ክፍል ወደሌላው ለዘመቻ መንቀሳቀሳቸው ነበር፡፡ በዚህም አንድ ሶስተኛው የአለም ህዝብ በዚህ በሽታ እንደተያዘ ይነገራል፤ በበሽታው ከተያዙት ውስጥ ደግሞ ከ10 እስከ 20 በመቶ የሚሆት ለሞት ተዳርገዋል፡፡

    የስፖኒሽ ፍሉ በሽታ ምልክቶች፡- ሳል፣ ከፍተኛ ትኩሳት፣ ነስር፣ የጆሮና የአንጀት መድማት፣ ተቅማጥ፣ የአይን ማስለቀስ፣ ውጋት እንዲሁም ከፍተኛ ደረጃ ላይ ሲደርስ የአእምሮ ህመም ያስከትላል፡፡ በዚህም በሽታው ኮሌራ ወይም ፈንጣጣ በሽታዎች ጋር ተተቀራራቢ ምልክቶችን ስለሚያሳይ ብዙ ያምታታ ነበር፡፡

    የኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክቶች

    የበሽታው አስገራሚ ባህሪ አንድ ሰው በበሽታው በተጠቃ በአምስት ቀን ውስጥ ወይ ይሞታል አልያም ከበሽታው ሙሉ ለሙሉ ይፈወሳል፡፡ ይህም እንደ ግለሰቡ የበሽታ መከላከል አቅም ይወሰናል፤ ቫይረሱ የተፈጥሮ የበሽታ የመከላከል አቅምን የሚያዳክም ሲሆን ጠንካራ የመከላከል አቅም ያለው ሰው ከአምስት ቀናት በላይ መቋቋም ስለሚያስችለው በስድስተኛው ቀን ፈውስ ያገኛል፡፡

    የስፓኒሽ ፍሉ ወረርሽኝ በአጭር ጊዜ ከሞላ ጎደል በመላው ዓለም ተሰራጭቶ ነበር

    ሲኖ ባይሎጂካ የተሰኛ የህክምና ጥናት ማዕከል ባደረገው ጥናት መሰረት በአሜሪካ እስከ 28 በመቶ የሚሆነው ህዝባ በበሽታው ተጠቅቶ ነበር፤ 675 ሺህ ገደማ የሚሆነው ህዝባ ደግሞ በበሽታው ሞታል፡፡ ወረርሽኙ በህንድ የከፋ ነበር፤ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት 17 ሚሊዮን ህንዳዊያን በበሽታው ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ በጃፓንም 23 ሚሊዮዮ ህዝቦችን ያጠቃው በሽታው 400 ሺህ ገደማ የሚሆኑትን ደግሞ ገድሏል፡፡ እንግሊዝ ሩብ ሚለዮን፣ ፈረንሳይ ደግሞ 400 ሺህ ዜጎቻቸውን በበሽታው አጥተዋል፡፡ እ.ኤ.አ ከጥር ወር 1918 ዓ.ም እስከ ታህሰስ 1920 ዓ.ም በመላው ዓለም ተንሰራፍቶ የቆየው የእንፍሉዌንዛ ወረርሽኝ አንድ መቶ ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ ፈጅቷል፤ የሟቾቹ ቁጥር እስከ 200 ሚሊዮን ይሆናል የሚሉ መረጃዎችም አሉ፡፡
    የወረርሽኙን ጉዳት የከፋ ያደረገው አምራች ዜጎችን በከፍተኛ ሁኔታ ማጥቃቱ ነበር፡፡ በበሽታው ከሞቱት መካከል ዕድሜያቸው ከ25 እስከ 34 ዓመት የሆኑ ወጣቶች አብዛኛውን ድርሻ ይወስዳሉ፤ በመሆኑም በሽታው ካደረሰው ሰብዓዊ ውድመት ባለፈ ጥሎት ያለፈው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠባሳ የከፋ ነበር፡፡

    ስፓኒሽ ፍሉ በአፍሪካ

    ወረርሽኙ በአፍሪካ በሁለት ዙር ነበር የታየው፤ የመጀመሪያው በፈረንጆቹ በ1918 ዓ.ም የጸደይና የበጋ ወራት ሲሆን ሁለተኛውና የከፋ ጉዳት ያደረሰው ደግሞ በበልግ ወራት የታየው ነበር፡፡ በሽታው ለመጀመረያ ጊዜ በአፍሪካ የታየው በወቅቱ የእግሊዝ ቅኝ ግዛት በነበረችው በሴራሊዮን ዋና ከተማ ፍሪታዎን ሲሆን በአጭር ጊዜ ወደሌሎች የአፍሪካ አገራት ተስፋፋ፡፡
    ሚስተር መሪ (Murray) የተባሉ አጥኚ Global Pandemic በተሰኘ ጥናታቸው እንዳሰፈሩት የበሽታው ስርጭት ከሰሃራ በታች በሚገኙ አገራት ላይ ሰፊ ነበር፤ በክፍለ አህጉሩ የተከሰተው የሞት መጠን በመላው ዓለም በበሽታው ከተከሰተው ሞት ውስጥ የ29 በመቶ ድርሻ አለው፡፡ በተለይም በምዕራብና ደቡባዊ አፍሪካ ጥፋቱ የከፋ ነበር፤ በጋና እስከ መቶ ሺህ ዜጎች እንዳለቁ ይገመታል፤ በምስራቅ አፍሪካም ቀላል የማባል ቁጥር ላቸው ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል፤ በእንግሊዝ ሶማሊ ሰባት በመቶ የሚሆኑ ህዝቦች በበሽታው ሲሞቱ፣ በኢትዮጵያም ከአርባ ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ህይወታቸውን አጥተዋል ፡፡

    ስፓኒሽ ፍሉ ወረርሽኝ በአፍሪካ ያኖረው ማህበራዊ እና የማህበረሰባዊ መስተጋብር አሻራ

    ከሰብዓዊ ውድመቱ ባለፈ ወረርሺኙ በአፍሪካ ከባድ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ አስከትላል፡፡ በጊዜው አጠራር ደቡብ ሮዴሺያ (የዛሬዋ ዚምባብዌ) አምራች የሰው ሀይል በበሽታው በመያዙ የወርቅ ማውጫ ማዕድናት እንዲዘጉ ሆኖ ነበር፤ በዚህም በማዕድን ዘረፉ ላይ የተንጠለጠለው የአገሪቱ ኢኮኖሚ ክፉኛ ተጎዳ፡፡ ወረርሽኙ በማላዊና በዛምቢያም ያደረሰው ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ ከፍ ያለ ነበር፡፡ በናይጀሪያም፣ በተለይ በደቡባዊ የአገሪቱ ክፍል በሽታው የከፋ ጥፋት በማድረሱ ተጠቅቶ ምርት በማሽቂልቆሉ ቀድሞ ለምግብነት የመይወውለው ካሳቫ ለምግብነት መዋል የጀመረው የወረርሽኙ መቀስቀስን ተከትሎ ነበር፤ በአነስተኛ ጉልበትና ብዙም ልፋት የማይጠይቀው ካሳቫ ተመራጭ ምግብ ስለነበር በጊዜው በስፋት መመረት ጀመረ፡፡

    የ1918ቱ የእንፍሉዌንዛ ወረርሽኝ በአፍሪካ ያስከተለው ማህበራዊ ቀውስ ቀላል አልነበረም፡፡ በሽታው ዘር፣ ቀለም፣ ሀይማኖት፣ የኢኮኖሚ ደረጃን ሳይለይ ሁሉንም ሰው የሚያጠቃ ቢሆንም ቅኝ ገዢዎች በሽታው ከጥቁር ህዝቦች የመጣ እንደሆነ በማናፈስ የዘር መድልዖ ለድረግ ተጠቅመውበታል፡፡ ይህ ችግር በተለይም በደቡብ አፍሪካ የጎላ ነበር፤ በዚህም ነጮችና ጥቁሮች ማንኛውንም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን በአንድ ላይ እንዳያደርጉ የሚደነግግ አዋጅ እንዲጸድቅ ተደረገ፡፡

    በቦትስዋናም በሽታው በርካታ ህጻናትን ወላጅ አልባ አድርጋል፡፡ በጋና የሆነው ደግሞ ትንሽ ለየት ያለ ነበር፤ በሽታው ተንሰራፍቶ በርካታ ሴቶች በመጠቃታቸው ከነባራዊው የጋናዊያን ባህልና ወግ ባፈነገጠ መልኩ ባሎች የሴቶች ድርሻ ተደርጎ ይወሰድ የነበረው የቤት ውስጥ ስራዎች መስራት ግድ ሆነባቸው፡፡ በዚህም ወንዶች ወደ ማዕድ ቤት ገብተው በቆሎ መፍጨት፣ ምግብ ማብሰል የመሳሰሉትን ስራዎች ይከውኑ ጀመር፡፡

    ስፓኒሽ ፍሉ በኢትዮጵያ

    በኢትዮጵያ በሽታው የታየው የመጀመሪያው የበሽታው ምልክት በዓለም ላይ ከታየበት ጥር 1910 ዓ.ም ከአስር ወራት በኋላ በህዳር ወር 1911 ዓ.ም ነው፡፡ ነገር ግን ቀደም ብሎ በሽታው መግባቱ አይቀርም በሚል ለቅድመ ትንቃቄ ስራዎች ለመስራት የሚያስችል ስራ እምብዛም ነበር፡፡

    የስፓኒሽ ፍሉ ተጠቂ ከሆኑት የአለም ህዝቦች መካከል ኢትዮጵያዊያን ይጠቀሳሉ

    በዚህ ረገድ ሊጠቀስ የሚችለው በኢትዮጵያ የኢጣሊያ ቆንሰላ ያደረገው ነገር ነበር፡፡ የታሪክ ምሁሩ ፕሮፌሰር ሪቻረድ ፓንክረስት እ.ኤ.አ በ1990 ዓ.ም ባሳተሙት An Introduction to the Medical History of Ethiopia በሚለው የምርምር ስራቸው እንደጻፉት በሽታው በውል ያልታወቀ ነበርና ምናልባትም የፈንጣጣ በሽታ ይሆናል በሚል በወቅቱ በኢጣሊያ ቆንስላ ትብብር በሀምሌ ወር 1910 ዓ.ም አስር ሺህ ዶዝ የፈንጣጣ ክትባት ወደ ኢትጵያ እንዲገባ ተደርጎ ነበር ፡፡ የሆነው ሆኖ ከዘመናዊ የህክምና ጋር ለማይተዋወቀው የኢትዮጵያ ህዝብም ወረርሽኙ ታላቅ መቅሰፍት ነበር፡፡ በሽታው ከቁጥጥር ውጭ ወጥቶ በመላው አገሪቱ ከባድ ዕልቂት ማስከተል ጀመረ፡፡ በተለይም ታላላቅ ኢትዮጵያዊያን በቫይረሱ መያዛቸውን ተከትሎ መረበሽን ፈጥሮ ነበር፡፡
    በበሽታው ከተጠቁ ታላላቅ የዘመኑ ሹመኞችና የቤተ መንግስት ሰዎች መካከል ራስ ተፈሪ መኮንን (ቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ) እና ባለቤታቸው ወ/ሮ አቴጌ መነን አስፋው ይገኙበታል፡፡ እንዲያውም የራስ ተፈሪና ቤተሰቦቻቸው ሀኪም የሆኑት ሊባኖሳዊው ዶክተር አሳድ ቼይባን ራሳቸው የበሽታው ተጠቂ ነበሩና የራስ ተፈሪን ቤተሰብ የሚያክም ጠፍቶ እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ፡፡

    ራስ ተፈሪ መኮንን እና ባለቤታቸው ወ/ሮ አቴጌ መነን አስፋው

    ከህዳር 7 እስከ ህዳር 20 1911 ዓ.ም ለአስራ አራት ቀናት ገደማ የቆየው በሽታው በህዳር ወር የተከሰተ በመሆኑም ህዝቡ የህዳር በሽታ እያለ ይጠራው ጀመር፡፡ ብላቴን ጌታ መርስዔ ሀዘን ወልደቂርቆስ የሃያኛው ክፍለ ዘመን መባቻ በተሰኘው መጽሀፋቸው እንዳሰፈሩት ወረርሽኙ እስከ አርባ ሺህ ኢትዮጵያዊንን ለሞት ዳርጋል፤ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ዘጠኝ ሺህ ዜጎች በበሽታው ሞተዋል፡፡
    በተለይም ህዳር 12 ቀን 1911 ዓ.ም በርካታ ኢትዮጵያዊያን የሞቱበት በመሆኑ ቀኑ በጽዳት ዘመቻ እንዲደረግ በአዋጅ ተነግሮ ስለነበር፣ ከዚያ በሃላ ባሉት ዓመታት ይህ ነገር እንደባህል ተወስዶ በየዓመቱ ህዳር 12 ቀን የጽዳት ዘመቻ ይደረግ ጀመር፤ ይህም በተለምዶ ህዳር ሲታጠን የምንለው ነው፡፡

    በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍል በየአመቱ ህዳር 12 ቀን ቆሻሻን ማቃጠል ማህበረሰባዊ ልማድ ነው

    በስፓኒሽ ፍሉ በሽታ የተደረጉ የህክምና ምርምሮች እና ውጤቶቻቸው

    ዶ/ር እናውጋው መሃሪ ፣ዶ/ር ክንፈ ገበየሁ እና ዶ/ር ዘርጋባቸው አስፋው የተባሉ የህክምና ባለሙያዎች በጋራ ያሰናዱትና በ2013 እ.ኤ.አ የታተመው The Manual of Ethiopian Medical History ላይ እንደሰፈረው የ1918ቱ የእንፍሉዌንዛ ወረርሽኝ ክትባት ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው በአሜሪካን አገር የቫንደርቢልት ዩኒቨርሲቲ (Vanderbilt University) ምሁራን ሲሆን ወቅቱም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ነበር፡፡ ከዚያ በሃላ ባሉት ዘመናት በየጊዜው የተሻሻሉ ክትባቶች በምርምር ተገኝተዋል፡፡
    በ1918 ዓ.ም እንደተከሰተው እንፍሉዌንዛ በወረርሽኝ መልክ ተከስቶ ባያውቅም ዛሬም ድረስ ግን የሰው ልጆች የጤና ፈተና መሆኑን አላቆመም፡፡እ.ኤ.አ በ2012 ዓ.ም ብቻ በመላው ዓለም አምስት መቶ ሺህ ሰዎች በበሽታው ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ በዘርፊ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት የእንፍልዌንዛ ክትባቶች የዋጋ ውድነት መፍትሄ ካላገኘ፣ ህዝቡ ስለ በሽታው በቂ ግንዛቤ ማስጨበጫ ካልተሰጠ፣ መንግስታት በሽታውን ለመከላከል ከፍ ያለ ትኩረት እስካልሰጡ ድረስ በእንፍሉዌንዛ ምክንያት የሚከሰተውን ሞት መቀነስ አዳጋች ነው፡፡